ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኢዮብ 30:6-12 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

6. በዐለት መካከል በምድር ጒድጓድ፣በደረቅ ሸለቆ ዋሻ ውስጥ ለመኖር ተገደዱ።

7. በጫካ ውስጥ ያናፋሉ፤በእሾሃማ ቍጥቋጦ መካከልም ይታፈጋሉ።

8. ስማቸው የማይታወቅ አልባሌ ናቸው፤ከምድሪቱም ተባረዋል።

9. “አሁን ግን ልጆቻቸው በዘፈን ይሣለቁብኛል፤በእነርሱም ዘንድ መተረቻ ሆኛለሁ።

10. ይጸየፉኛል ወደ እኔም አይቀርቡም፤ያለ ምንም ይሉኝታ በፊቴ ይተፋሉ።

11. እግዚአብሔር የቀስቴን አውታር ስላላላውና በመከራም ስለ መታኝ፣በፊቴ መቈጠብን ትተዋል።

12. በቀኜ በኩል ባለጌዎች ሆ! ብለው ተነሡብኝ፤ለእግሬም ወጥመድ ዘረጉ፤የዐፈር ድልድልም አዘጋጁብኝ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኢዮብ 30