ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኢዮብ 30:20-30 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

20. “እግዚአብሔር ሆይ፤ ወደ አንተ ጮኽሁ፤ ነገር ግን አልመለስህልኝም፤በፊትህም ቆምሁ፤ አንተ ግን ዝም አልኸኝ።

21. ተመልሰህ ጨካኝ ሆንህብኝ፤በክንድህም ብርታት አስጨነቅኸኝ።

22. ወደ ላይ ነጥቀህ በነፋስ ፊት አበረርኸኝ፤በዐውሎ ነፋስም ወዲያ ወዲህ ወዘወዝኸኝ።

23. ለሕያዋን ሁሉ ወደ ተመደበው ስፍራ፣ወደ ሞት እንደምታወርደኝ ዐውቃለሁ።

24. “የተጐዳ ሰው ተጨንቆ ድረሱልኝ ብሎ ሲጮኽ፣በእርግጥ ክንዱን የሚያነሣበት ማንም የለም።

25. በመከራ ውስጥ ላሉት አላለቀስሁምን?ለድኾችስ ነፍሴ አላዘነችምን?

26. ነገር ግን መልካም ስጠብቅ፣ ክፉ ነገር ደረሰብኝ፤ብርሃንንም ስጠባበቅ፣ ጨለማ መጣብኝ።

27. በውስጤ ያለው ነውጥ አላቋረጠም፤የመከራ ዘመንም መጣብኝ።

28. በፀሓይ አይደለም እንጂ፣ ጠቋቍሬ እዞራለሁ፤በጉባኤ መካከል ቆሜ ለርዳታ እጮኻለሁ።

29. የቀበሮች ወንድም፣የጒጒቶችም ባልንጀራ ሆኛለሁ።

30. ቈዳዬ ጠቍሮ ተቀረፈ፤ዐጥንቴም በትኵሳት ነደደ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኢዮብ 30