ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኢዮብ 30:17-25 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

17. ደዌ በሌሊት ዐጥንቴን ይበሳል፤የሚቈረጥመኝም ፋታ አይሰጠኝም።

18. እግዚአብሔር በታላቅ ኀይሉ ልብሴን ጨምድዶአል፤በልብሴም ክሳድ አንቆ ይዞኛል።

19. እርሱ ጭቃ ውስጥ ጥሎኛል፤እኔም ከዐፈርና ከዐመድ አልተሻልሁም።

20. “እግዚአብሔር ሆይ፤ ወደ አንተ ጮኽሁ፤ ነገር ግን አልመለስህልኝም፤በፊትህም ቆምሁ፤ አንተ ግን ዝም አልኸኝ።

21. ተመልሰህ ጨካኝ ሆንህብኝ፤በክንድህም ብርታት አስጨነቅኸኝ።

22. ወደ ላይ ነጥቀህ በነፋስ ፊት አበረርኸኝ፤በዐውሎ ነፋስም ወዲያ ወዲህ ወዘወዝኸኝ።

23. ለሕያዋን ሁሉ ወደ ተመደበው ስፍራ፣ወደ ሞት እንደምታወርደኝ ዐውቃለሁ።

24. “የተጐዳ ሰው ተጨንቆ ድረሱልኝ ብሎ ሲጮኽ፣በእርግጥ ክንዱን የሚያነሣበት ማንም የለም።

25. በመከራ ውስጥ ላሉት አላለቀስሁምን?ለድኾችስ ነፍሴ አላዘነችምን?

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኢዮብ 30