ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኢዮብ 30:13-17 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

13. መንገድ ዘጉብኝ፤የሚገታቸው ሳይኖር፣ሊያጠፉኝ ተነሡ።

14. በሰፊ ንቃቃት ውስጥ እንደሚመጣ ሰው መጡብኝ፤በፍርስራሽም መካከል እየተንከባለሉ ደረሱብኝ።

15. በድንጋጤ ተውጫለሁ፤ክብሬ በነፋስ እንደሚወሰድ ተወስዶአል፤በሰላም መኖሬም እንደ ደመና እልም ብሎ ጠፍቶአል።

16. “አሁን ነፍሴ በውስጤ አለቀች፤የመከራ ዘመንም ይዞኛል።

17. ደዌ በሌሊት ዐጥንቴን ይበሳል፤የሚቈረጥመኝም ፋታ አይሰጠኝም።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኢዮብ 30