ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኢዮብ 30:1-7 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. “አሁን ግን በዕድሜ ከእኔ የሚያንሱ፣ከመንጋዬ ጠባቂ ውሾች ጋር እንዳይቀመጡ፣አባቶቻቸውን የናቅኋቸው፣እነዚህ ይሣለቁብኛል።

2. ጒልበት የከዳቸው፤የክንዳቸው ብርታት ምን ፋይዳ ይሞላልኝ ነበር?

3. ከችጋርና ከራብ የተነሣ ጠወለጉ፤ሰው በማይኖርበት በረሓ፣በደረቅም ምድር በሌሊት ተንከራተቱ።

4. ከቍጥቋጦ ምድር ጨው ጨው የሚል አትክልት ለቀሙ፤ምግባቸውም የክትክታ ሥር ነበር።

5. ከኅብረተ ሰቡ ተለይተው ተባረሩ፤ሰዎች እንደ ሌባ ይጮኹባቸዋል።

6. በዐለት መካከል በምድር ጒድጓድ፣በደረቅ ሸለቆ ዋሻ ውስጥ ለመኖር ተገደዱ።

7. በጫካ ውስጥ ያናፋሉ፤በእሾሃማ ቍጥቋጦ መካከልም ይታፈጋሉ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኢዮብ 30