ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኢዮብ 29:6-11 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

6. መንገዴ በቅቤ የራሰ ነበር፤ዐለቱም የወይራ ዘይት ያመነጭልኝ ነበር።

7. “ወደ ከተማዪቱ በር ብቅ ባልሁ ጊዜ፣በአደባባይዋም በወንበር በተቀመጥሁ ጊዜ፣

8. ጐበዛዝት አይተውኝ ገለል ይሉ፣ሽማግሌዎችም ተነሥተው ይቆሙ ነበር።

9. የሰፈሩ ታላላቅ ሰዎች ከመናገር ይቈጠቡ፣እጃቸውንም በአፋቸው ላይ ይጭኑ ነበር፤

10. የመኳንንት ድምፅ ጸጥ ይል፣ምላሳቸውም ከላንቃቸው ጋር ይጣበቅ ነበር፤

11. የሰሙኝ ሁሉ ያሞጋግሱኝ፣ያዩኝም ያመሰግኑኝ ነበር፤

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኢዮብ 29