ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኢዮብ 29:13-24 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

13. በሞት አፋፍ ላይ የነበረ መርቆኛል፤የመበለቲቱንም ልብ አሳርፌአለሁ።

14. ጽድቅን እንደ ልብስ ለበስሁ፤ፍትሕም መጐናጸፊያዬና ጥምጥሜ ነበር።

15. ለዕዉራን ዐይን፣ለአንካሶችም እግር ነበርሁ።

16. ለችግረኛው አባት፣ለባይተዋሩ ተሟጋች ነበርሁ።

17. የኀጢአተኛውን ክራንቻ ሰበርሁ፤የነጠቀውንም ከጥርሶቹ አስጣልሁ።

18. “እኔም በልቤ እንዲህ አልሁ፤ ‘ዘመኔ እንደ አሸዋ በዝቶ፣በቤቴ ተደላድዬ እሞታለሁ፤

19. ሥሬ ወደ ውሃ ይዘረጋል፤ጠልም በቅርንጫፌ ላይ ያድራል፤

20. ክብሬ በውስጤ አዲስ እንደሆነ፣ቀስትም በእጄ እንደ በረታ ይኖራል።’

21. “ሰዎች ምክሬን በጸጥታ በመጠባበቅ፣በጒጒት አዳመጡኝ።

22. እኔ ከተናገርሁ በኋላ፣ የሚናገር ሰው አልነበረም፤ቃሌም እየተንጠባጠበ በጆሯቸው ይገባ ነበር።

23. ዝናብ እንደሚጠብቅ ሰው ጠበቁኝ፤ቃሌንም እንደ በልግ ዝናብ ጠጡ፤

24. በሣቅሁላቸው ጊዜ እውነት አልመሰላቸውም፤የፊቴም ብርሃን ብርቃቸው ነበር።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኢዮብ 29