ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኢዮብ 29:12-16 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

12. ለርዳታ የሚጮኸውን ችግረኛ፣ድኻ ዐደጉንም ታድጌአለሁና።

13. በሞት አፋፍ ላይ የነበረ መርቆኛል፤የመበለቲቱንም ልብ አሳርፌአለሁ።

14. ጽድቅን እንደ ልብስ ለበስሁ፤ፍትሕም መጐናጸፊያዬና ጥምጥሜ ነበር።

15. ለዕዉራን ዐይን፣ለአንካሶችም እግር ነበርሁ።

16. ለችግረኛው አባት፣ለባይተዋሩ ተሟጋች ነበርሁ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኢዮብ 29