ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኢዮብ 27:9-16 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

9. በውኑ መከራ በገጠመው ጊዜ፣እግዚአብሔር ጩኸቱን ይሰማልን?

10. ሁሉን በሚችል አምላክ ደስ ይለዋልን?ዘወትርስ እግዚአብሔርን ይጠራልን?

11. “ስለ እግዚአብሔር ክንድ አስተምራችኋለሁ፤የሁሉን ቻዩንም አምላክ ዕቅድ አልሸሽግም።

12. ሁላችሁ ይህን አይታችኋል፤ታዲያ፣ ይህ ከንቱ ንግግር ምንድን ነው?

13. “እግዚአብሔር ለክፉው የመደበው ዕድል ፈንታ፣ግፈኛም ሁሉን ከሚችል አምላክ የሚቀበለው ቅርስ ይህ ነው፦

14. ልጆቹ የቱንም ያህል ቢበዙም ለሰይፍ ይዳረጋሉ፤ዘሩም ጠግቦ አያድርም።

15. የተረፉለትም በመቅሠፍት አልቀው ይቀበራሉ፤መበለቶቻቸውም አያለቅሱላቸውም።

16. ብርን እንደ ዐፈር ቢከምር፣ልብስንም እንደ ሸክላ ጭቃ ቢያከማች፣

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኢዮብ 27