ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኢዮብ 27:17-22 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

17. እርሱ ያከማቸውን ጻድቃን ይለብሱታል፤ብሩንም ንጹሓን ይከፋፈሉታል።

18. የሚሠራው ቤት እንደ ሸረሪት ድር፣እህል ጠባቂም እንደ ቀለሰው መጠለያ ነው።

19. ሀብታም ሆኖ ይተኛል፤ ዘለቄታ ግን የለውም፤ዐይኑን በገለጠ ጊዜ ሀብቱ ሁሉ በቦታው የለም።

20. ድንጋጤ እንደ ጐርፍ ድንገት ያጥለቀልቀዋል፤ዐውሎ ነፋስም በሌሊት ይዞት ይሄዳል።

21. የምሥራቅ ነፋስ ይወስደዋል፤ እርሱም አይገኝም፤ከስፍራውም ይጠርገዋል።

22. ከነፋሱ ብርታት ለማምለጥ ይሮጣል፤ነገር ግን እየተወረወረ ያለ ርኅራኄ ይደርስበታል፤

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኢዮብ 27