ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኢዮብ 27:16-21 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

16. ብርን እንደ ዐፈር ቢከምር፣ልብስንም እንደ ሸክላ ጭቃ ቢያከማች፣

17. እርሱ ያከማቸውን ጻድቃን ይለብሱታል፤ብሩንም ንጹሓን ይከፋፈሉታል።

18. የሚሠራው ቤት እንደ ሸረሪት ድር፣እህል ጠባቂም እንደ ቀለሰው መጠለያ ነው።

19. ሀብታም ሆኖ ይተኛል፤ ዘለቄታ ግን የለውም፤ዐይኑን በገለጠ ጊዜ ሀብቱ ሁሉ በቦታው የለም።

20. ድንጋጤ እንደ ጐርፍ ድንገት ያጥለቀልቀዋል፤ዐውሎ ነፋስም በሌሊት ይዞት ይሄዳል።

21. የምሥራቅ ነፋስ ይወስደዋል፤ እርሱም አይገኝም፤ከስፍራውም ይጠርገዋል።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኢዮብ 27