ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኢዮብ 27:14-23 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

14. ልጆቹ የቱንም ያህል ቢበዙም ለሰይፍ ይዳረጋሉ፤ዘሩም ጠግቦ አያድርም።

15. የተረፉለትም በመቅሠፍት አልቀው ይቀበራሉ፤መበለቶቻቸውም አያለቅሱላቸውም።

16. ብርን እንደ ዐፈር ቢከምር፣ልብስንም እንደ ሸክላ ጭቃ ቢያከማች፣

17. እርሱ ያከማቸውን ጻድቃን ይለብሱታል፤ብሩንም ንጹሓን ይከፋፈሉታል።

18. የሚሠራው ቤት እንደ ሸረሪት ድር፣እህል ጠባቂም እንደ ቀለሰው መጠለያ ነው።

19. ሀብታም ሆኖ ይተኛል፤ ዘለቄታ ግን የለውም፤ዐይኑን በገለጠ ጊዜ ሀብቱ ሁሉ በቦታው የለም።

20. ድንጋጤ እንደ ጐርፍ ድንገት ያጥለቀልቀዋል፤ዐውሎ ነፋስም በሌሊት ይዞት ይሄዳል።

21. የምሥራቅ ነፋስ ይወስደዋል፤ እርሱም አይገኝም፤ከስፍራውም ይጠርገዋል።

22. ከነፋሱ ብርታት ለማምለጥ ይሮጣል፤ነገር ግን እየተወረወረ ያለ ርኅራኄ ይደርስበታል፤

23. እጁንም እያጨበጨበ ያሾፍበታል፤በፉጨትም ከስፍራው ያሽቀነጥረዋል።”

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኢዮብ 27