ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኢዮብ 27:1-13 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. ኢዮብም እንዲህ ሲል ንግግሩን ቀጠለ፤

2. “ፍትሕ የነሣኝ ሕያው እግዚአብሔርን!ነፍሴንም መራራ ያደረጋት፣ ሁሉን ቻይ አምላክን!

3. በውስጤ የሕይወት እስትንፋስ፣በአፍንጫዬም ውስጥ የእግዚአብሔር መንፈስ እስካለ ድረስ፣

4. ከንፈሬ ኀጢአትን አትናገርም፤አንደበቴም ሽንገላ አይወጣውም።

5. እናንተን እንደ ቅኖች መቍጠር፣የማላደርገው ነገር ነው፤ ጨዋነቴንም እስክሞት ድረስ አልጥልም።

6. ጽድቄን አጥብቄ እይዛለሁ፤ አልለቀውምም፤በዘመኔም ሁሉ ኅሊናዬ አይወቅሰኝም።

7. “ጠላቴ እንደ በደለኛ፣ባላንጣዬም እንደ ክፉ ይሁን።

8. እግዚአብሔር ሲያስወግደው፣ነፍሱንም ሲወስድበት ዐመፀኛ ምን ተስፋ አለው?

9. በውኑ መከራ በገጠመው ጊዜ፣እግዚአብሔር ጩኸቱን ይሰማልን?

10. ሁሉን በሚችል አምላክ ደስ ይለዋልን?ዘወትርስ እግዚአብሔርን ይጠራልን?

11. “ስለ እግዚአብሔር ክንድ አስተምራችኋለሁ፤የሁሉን ቻዩንም አምላክ ዕቅድ አልሸሽግም።

12. ሁላችሁ ይህን አይታችኋል፤ታዲያ፣ ይህ ከንቱ ንግግር ምንድን ነው?

13. “እግዚአብሔር ለክፉው የመደበው ዕድል ፈንታ፣ግፈኛም ሁሉን ከሚችል አምላክ የሚቀበለው ቅርስ ይህ ነው፦

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኢዮብ 27