ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኢዮብ 26:11-14 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

11. የሰማይ ምሰሶዎች ይንቀጠቀጣሉ፤በተግሣጹም ይደነግጣሉ።

12. በኀይሉ ባሕርን ያናውጣል፤በጥበቡም ረዓብን ይቈራርጣል።

13. በእስትንፋሱ ሰማያትን አጠራ፤እጁም ተወርዋሪውን እባብ ወጋች።

14. እነዚህ የሥራው ዳር ዳር ናቸው፤ስለ እርሱ የሰማነው ምንኛ አነስተኛ ነው!የኀይሉንስ ነጐድጓድ ማን ሊያስተውል ይችላል?”

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኢዮብ 26