ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኢዮብ 26:1-7 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. ኢዮብም እንዲህ ሲል መለሰ፤

2. “ኀይል የሌለውን ምንኛ ረዳኸው!ደካማውንስ ምንኛ አዳንኸው!

3. ጥበብ የሌለውን ምንኛ መከርኸው!ታላቅ ዕውቀትንስ ምንኛ ገለጥህለት!

4. ይህን ቃል እንድትናገር የረዳህ ማን ነው?የማንስ መንፈስ በአንደበትህ ተጠቀመ?

5. “ከውሆችና በውስጣቸው ከሚኖሩ በታች ያሉ፣የሙታን መንፈስ በጭንቅ ላይ ናቸው።

6. ሲኦል በእግዚአብሔር ፊት ዕራቍቷን ናት፤የጥፋትንም ስፍራ የሚጋርድ የለም።

7. የሰሜንን ሰማይ በሕዋው ላይ ዘረጋው፤ምድርንም እንዲያው በባዶው ላይ አንጠለጠላት።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኢዮብ 26