ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኢዮብ 23:5-9 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

5. የሚመልስልኝ ቃል ምን እንደሆነ ባወቅሁ ነበር፤የሚለኝንም ባስተዋልሁ ነበር።

6. በታላቅ ኀይሉ ከእኔ ጋር ይሟገት ይሆን?አይደለም፤ ይልቁን ያደምጠኛል።

7. ቅን ሰው ጒዳዩን በእርሱ ፊት ያቀርባል፤እኔም ከፈራጄ ለዘላለም ነጻ እሆናለሁ።

8. “ዳሩ ግን ወደ ምሥራቅ ብሄድ፣ በዚያ የለም፤ወደ ምዕራብም ብሄድ፣ እርሱን አላገኘውም፤

9. በሰሜን እየሠራ ሳለ አላየውም፤ወደ ደቡብ በሚዞርበት ጊዜ ደብዛው አይገኝም።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኢዮብ 23