ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኢዮብ 23:4-14 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

4. ጒዳዬን በፊቱ አቀርብ ነበር፤አፌንም በሙግት እሞላው ነበር።

5. የሚመልስልኝ ቃል ምን እንደሆነ ባወቅሁ ነበር፤የሚለኝንም ባስተዋልሁ ነበር።

6. በታላቅ ኀይሉ ከእኔ ጋር ይሟገት ይሆን?አይደለም፤ ይልቁን ያደምጠኛል።

7. ቅን ሰው ጒዳዩን በእርሱ ፊት ያቀርባል፤እኔም ከፈራጄ ለዘላለም ነጻ እሆናለሁ።

8. “ዳሩ ግን ወደ ምሥራቅ ብሄድ፣ በዚያ የለም፤ወደ ምዕራብም ብሄድ፣ እርሱን አላገኘውም፤

9. በሰሜን እየሠራ ሳለ አላየውም፤ወደ ደቡብ በሚዞርበት ጊዜ ደብዛው አይገኝም።

10. ግን እኔ የምሄድበትን መንገድ ያውቃል፤ከፈተነኝም በኋላ እንደ ወርቅ እወጣለሁ።

11. እግሮቼ እርምጃውን በጥብቅ ተከታትለዋል፤ፈቀቅ ሳልል መንገዱን ጠብቄአለሁ።

12. ከአፉ ከወጣው ትእዛዝ አልራቅሁም፣የአንደበቱን ቃል ከዕለት እንጀራዬ አብልጬ ይዣለሁ።

13. “እርሱ ግን ራሱን ችሎ ብቻውን የሚኖር ነው፤ የሚቋቋመውስ ማን ነው?እርሱ የፈቀደውን ያደርጋል።

14. በእኔ ላይ የወሰነውን ይፈጽማል፤ይህን የመሰለ ዕቅድም ገና ብዙ አለው።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኢዮብ 23