ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኢዮብ 23:13-16 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

13. “እርሱ ግን ራሱን ችሎ ብቻውን የሚኖር ነው፤ የሚቋቋመውስ ማን ነው?እርሱ የፈቀደውን ያደርጋል።

14. በእኔ ላይ የወሰነውን ይፈጽማል፤ይህን የመሰለ ዕቅድም ገና ብዙ አለው።

15. በፊቱ የደነገጥሁትም ለዚህ ነው፤ይህን ሁሉ ሳስብ እፈራለሁ።

16. እግዚአብሔር ልቤን አባባው፤ሁሉንም የሚችል አምላክ አስደነገጠኝ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኢዮብ 23