ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኢዮብ 23:1-8 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. ኢዮብም እንዲህ ሲል መለሰ፤

2. “ዛሬም ሐዘኔ መራራ ነው፤እያቃሰትሁ እንኳ እጁ በላዬ ከብዳለች።

3. እርሱን የት እንደማገኘው ባወቅሁ፤ወደ መኖሪያውም መሄድ በቻልሁ!

4. ጒዳዬን በፊቱ አቀርብ ነበር፤አፌንም በሙግት እሞላው ነበር።

5. የሚመልስልኝ ቃል ምን እንደሆነ ባወቅሁ ነበር፤የሚለኝንም ባስተዋልሁ ነበር።

6. በታላቅ ኀይሉ ከእኔ ጋር ይሟገት ይሆን?አይደለም፤ ይልቁን ያደምጠኛል።

7. ቅን ሰው ጒዳዩን በእርሱ ፊት ያቀርባል፤እኔም ከፈራጄ ለዘላለም ነጻ እሆናለሁ።

8. “ዳሩ ግን ወደ ምሥራቅ ብሄድ፣ በዚያ የለም፤ወደ ምዕራብም ብሄድ፣ እርሱን አላገኘውም፤

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኢዮብ 23