ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኢዮብ 22:24-30 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

24. የወርቅህን አንኳር ትቢያ ላይ፣የኦፊር ወርቅህንም ጥልቅ ሸለቆ ውስጥ ብትጥለው፣

25. ሁሉን ቻዩ አምላክ ወርቅ ይሆንልሃል፤ምርጥ ብር ይሆንልሃል።

26. በዚያ ጊዜ ሁሉን በሚችል አምላክ ደስ ይልሃል፤ፊትህንም ወደ እግዚአብርሔር ታቀናለህ።

27. ወደ እርሱ ትጸልያለህ፤ እርሱም ይሰማሃል፤አንተም ስእለትህን ትሰጣለህ።

28. ያሰብኸው ይከናወንልሃል፤በመንገድህም ላይ ብርሃን ይበራል።

29. ሰዎች ቢዋረዱና አንተ፣ ‘ከፍ አድርጋቸው’ ብትል፣እርሱ ዝቅ ያሉትን ያድናል፤

30. በጎ ያልሆነውን ሰው እንኳ፣ከአንተ እጅ ንጽሕና የተነሣ ያድነዋል።”

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኢዮብ 22