ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኢዮብ 22:22-28 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

22. ምክርን ከአፉ ተቀበል፤ቃሉንም በልብህ አኑር።

23. ሁሉን ወደሚችል አምላክ ብትመለስ ትጠገናለህ፤ክፋትን ከድንኳንህ ብታርቅ፣

24. የወርቅህን አንኳር ትቢያ ላይ፣የኦፊር ወርቅህንም ጥልቅ ሸለቆ ውስጥ ብትጥለው፣

25. ሁሉን ቻዩ አምላክ ወርቅ ይሆንልሃል፤ምርጥ ብር ይሆንልሃል።

26. በዚያ ጊዜ ሁሉን በሚችል አምላክ ደስ ይልሃል፤ፊትህንም ወደ እግዚአብርሔር ታቀናለህ።

27. ወደ እርሱ ትጸልያለህ፤ እርሱም ይሰማሃል፤አንተም ስእለትህን ትሰጣለህ።

28. ያሰብኸው ይከናወንልሃል፤በመንገድህም ላይ ብርሃን ይበራል።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኢዮብ 22