ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኢዮብ 22:1-10 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. ቴማናዊውም ኤልፋዝ እንዲህ ሲል መለሰ፤

2. “ሰው እግዚአብሔርን ሊጠቅም ይችላልን?ጠቢብ እንኳ ቢሆን ምን ይጠቅመዋል?

3. አንተ ጻድቅ ብትሆን ሁሉን የሚችለውን አምላክ ምን ደስ ታሰኘዋለህ?መንገድህ ያለ ነቀፋ ቢሆንስ የሚተርፈው ምንድን ነው?

4. “እርሱ የሚገሥጽህ፣ፍርድ ቤትም የሚያቀርብህ ስለምትፈራው ነውን?

5. ክፋትህ ታላቅ፣ኀጢአትህ ፍጻሜ የሌለው አይደለምን?

6. ያለ አንዳች ምክንያት ከወንድሞችህ መያዣ ወስደሃል፤ሰዎችን ገፈህ፣ ያለ ልብስ ዕራቍታቸውን አስቀርተሃል።

7. የዛሉትን ውሃ አላጠጣህም፤የተራቡትንም ምግብ ከልክለሃል።

8. ባለ ርስትና ኀያል፣በእርሱም የምትኖር ክቡር ሰው ብትሆንም፣

9. መበለቶችን ባዶ እጃቸውን ሰደሃል፤የድኻ ዐደጎችንም ክንድ ሰብረሃል።

10. ድንገተኛ አደጋ ያናወጠህ፤ወጥመድም ዙሪያህን የከበበህ ለዚህ ነው።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኢዮብ 22