ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኢዮብ 21:8-19 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

8. ዘራቸው በዐይናቸው ፊት፣ልጆቻቸውም በዙሪያቸው ጸንተው ሲኖሩ ያያሉ፤

9. ቤታቸው ያለ ሥጋት በሰላም ይኖራል፤የእግዚአብሔርም በትር የለባቸውም።

10. ኮርማቸው ዘሩ በከንቱ አይወድቅም፤ያስረግዛል፤ ላማቸውም ሳትጨነግፍ ትወልዳለች።

11. ልጆቻቸውን እንደ በግ መንጋ ያሰማራሉ፤ሕፃናታቸውም ይቦርቃሉ።

12. በከበሮና በክራር ይዘፍናሉ፤በዋሽንትም ድምፅ ይፈነጫሉ።

13. ዕድሜያቸውን በተድላ ያሳልፋሉ፤በሰላምም ወደ መቃብር ይወርዳሉ።

14. እግዚአብሔርንም እንዲህ ይሉታል፤ ‘አትድረስብን!መንገድህንም ማወቅ አንፈልግም።

15. እናገለግለው ዘንድ፣ ሁሉን ቻይ አምላክ ማን ነው?ወደ እርሱ ብንጸልይስ ምን እናገኛለን?’

16. ይሁንና ብልጽግናቸው በእጃቸው አይደለም፤ከኀጢአተኞች ምክር እርቃለሁ።

17. “የኀጢአተኞች መብራት የጠፋው ስንት ጊዜ ነው?የእግዚአብሔር ቍጣ መከራ የመጣባቸው፣መቅሠፍትም የደረሰባቸው ስንት ጊዜ ነው?

18. በነፋስ ፊት እንዳለ ገለባ፣በዐውሎ ነፋስም እንደ ተወሰደ ዕብቅ የሆኑት ስንት ጊዜ ነው?

19. እናንተ፣ ‘እግዚአብሔር የሰውን ቅጣት ለልጆቹ ያከማቻል’ ትላላችሁ፤ነገር ግን ያውቀው ዘንድ ለሰውየው ለራሱ ይክፈለው፤

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኢዮብ 21