ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኢዮብ 21:4-13 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

4. “በውኑ ቅርታዬ በሰው ላይ ነውን?ትዕግሥት ማጣትስ አይገባኝምን?

5. ተመልከቱኝና ተገረሙ፤አፋችሁን በእጃችሁ ለጒሙ።

6. ስለዚህ ነገር ባሰብሁ ቍጥር እደነግጣለሁ፤ሰውነቴም በፍርሀት ይንቀጠቀጣል።

7. ኀጢአተኞች ለምን በሕይወት ይኖራሉ?ለምን ለእርጅና ይበቃሉ? ለምንስ እያየሉ ይሄዳሉ?

8. ዘራቸው በዐይናቸው ፊት፣ልጆቻቸውም በዙሪያቸው ጸንተው ሲኖሩ ያያሉ፤

9. ቤታቸው ያለ ሥጋት በሰላም ይኖራል፤የእግዚአብሔርም በትር የለባቸውም።

10. ኮርማቸው ዘሩ በከንቱ አይወድቅም፤ያስረግዛል፤ ላማቸውም ሳትጨነግፍ ትወልዳለች።

11. ልጆቻቸውን እንደ በግ መንጋ ያሰማራሉ፤ሕፃናታቸውም ይቦርቃሉ።

12. በከበሮና በክራር ይዘፍናሉ፤በዋሽንትም ድምፅ ይፈነጫሉ።

13. ዕድሜያቸውን በተድላ ያሳልፋሉ፤በሰላምም ወደ መቃብር ይወርዳሉ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኢዮብ 21