ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኢዮብ 21:27-32 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

27. “እነሆ፣ ምክራችሁን፣በእኔ ላይ ያሤራችሁትንም ተረድቻለሁ።

28. እናንተ፣ ‘የትልቁ ሰው ቤት፣ኀጢአተኛውም የኖረበት ድንኳን የት አለ?’ አላችሁ፤

29. መንገደኞችን አልጠየቃችሁምን?የነገሯችሁንስ ነገር በጥሞና አላዳመጣችሁምን?

30. ክፉ ሰው በመቅሠፍት ቀን እንደሚጠበቅ፣በቍጣም ቀን እንደሚተርፍ አታውቁምን?

31. ተግባሩን ፊት ለፊት የሚነግረው ማን ነው?የእጁንስ ማን ይሰጠዋል?

32. ወደ መቃብር ይወስዱታል፤ለመቃብሩም ጠባቂ ይደረግለታል።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኢዮብ 21