ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኢዮብ 21:26-34 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

26. ሁለቱም በዐፈር ውስጥ አንድ ላይ ይተኛሉ፤ትልም ይወርሳቸዋል።

27. “እነሆ፣ ምክራችሁን፣በእኔ ላይ ያሤራችሁትንም ተረድቻለሁ።

28. እናንተ፣ ‘የትልቁ ሰው ቤት፣ኀጢአተኛውም የኖረበት ድንኳን የት አለ?’ አላችሁ፤

29. መንገደኞችን አልጠየቃችሁምን?የነገሯችሁንስ ነገር በጥሞና አላዳመጣችሁምን?

30. ክፉ ሰው በመቅሠፍት ቀን እንደሚጠበቅ፣በቍጣም ቀን እንደሚተርፍ አታውቁምን?

31. ተግባሩን ፊት ለፊት የሚነግረው ማን ነው?የእጁንስ ማን ይሰጠዋል?

32. ወደ መቃብር ይወስዱታል፤ለመቃብሩም ጠባቂ ይደረግለታል።

33. የሸለቈው ዐፈር ምቹ ይሆንለታል፤ሰው ሁሉ ይከተለዋል፤ስፍር ቍጥር የሌለው ሕዝብ በፊቱ ይሄዳል።

34. “መልሳችሁ ከሐሰት በስተቀር ሌላ አይገኝበትም፤ታዲያ፣ በማይረባ ነገር እንዴት ልታጽናኑኝ ትችላላችሁ!”

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኢዮብ 21