ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኢዮብ 21:16-31 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

16. ይሁንና ብልጽግናቸው በእጃቸው አይደለም፤ከኀጢአተኞች ምክር እርቃለሁ።

17. “የኀጢአተኞች መብራት የጠፋው ስንት ጊዜ ነው?የእግዚአብሔር ቍጣ መከራ የመጣባቸው፣መቅሠፍትም የደረሰባቸው ስንት ጊዜ ነው?

18. በነፋስ ፊት እንዳለ ገለባ፣በዐውሎ ነፋስም እንደ ተወሰደ ዕብቅ የሆኑት ስንት ጊዜ ነው?

19. እናንተ፣ ‘እግዚአብሔር የሰውን ቅጣት ለልጆቹ ያከማቻል’ ትላላችሁ፤ነገር ግን ያውቀው ዘንድ ለሰውየው ለራሱ ይክፈለው፤

20. ዐይኖቹ የራሱን ውድቀት ይዩ፤ሁሉን ከሚችል አምላክ ቍጣ ይጠጣ።

21. ሰው ወራቱ በተገባደደ ጊዜ፣ለቀሪ ቤተ ሰቡምን ይገደዋል?

22. “ከፍ ባሉት ላይ ለሚፈርድ አምላክ፣ዕውቀትን ሊያስተምረው የሚችል አለን?

23. አንድ ሰው በፍጹም ተድላ ደስታ እየኖረ፣በሙሉ ብርታቱም እያለ ይሞታል፤

24. ሰውነቱ በምቾት፣ዐጥንቱም በስብ ተሞልቶ እያለ በሞት ይለያል።

25. ሌላው ሰው ደግሞ አንዳች መልካም ነገር ሳያይ፣በተመረረች ነፍስ ይሞታል፤

26. ሁለቱም በዐፈር ውስጥ አንድ ላይ ይተኛሉ፤ትልም ይወርሳቸዋል።

27. “እነሆ፣ ምክራችሁን፣በእኔ ላይ ያሤራችሁትንም ተረድቻለሁ።

28. እናንተ፣ ‘የትልቁ ሰው ቤት፣ኀጢአተኛውም የኖረበት ድንኳን የት አለ?’ አላችሁ፤

29. መንገደኞችን አልጠየቃችሁምን?የነገሯችሁንስ ነገር በጥሞና አላዳመጣችሁምን?

30. ክፉ ሰው በመቅሠፍት ቀን እንደሚጠበቅ፣በቍጣም ቀን እንደሚተርፍ አታውቁምን?

31. ተግባሩን ፊት ለፊት የሚነግረው ማን ነው?የእጁንስ ማን ይሰጠዋል?

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኢዮብ 21