ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኢዮብ 21:13-18 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

13. ዕድሜያቸውን በተድላ ያሳልፋሉ፤በሰላምም ወደ መቃብር ይወርዳሉ።

14. እግዚአብሔርንም እንዲህ ይሉታል፤ ‘አትድረስብን!መንገድህንም ማወቅ አንፈልግም።

15. እናገለግለው ዘንድ፣ ሁሉን ቻይ አምላክ ማን ነው?ወደ እርሱ ብንጸልይስ ምን እናገኛለን?’

16. ይሁንና ብልጽግናቸው በእጃቸው አይደለም፤ከኀጢአተኞች ምክር እርቃለሁ።

17. “የኀጢአተኞች መብራት የጠፋው ስንት ጊዜ ነው?የእግዚአብሔር ቍጣ መከራ የመጣባቸው፣መቅሠፍትም የደረሰባቸው ስንት ጊዜ ነው?

18. በነፋስ ፊት እንዳለ ገለባ፣በዐውሎ ነፋስም እንደ ተወሰደ ዕብቅ የሆኑት ስንት ጊዜ ነው?

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኢዮብ 21