ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኢዮብ 20:8-14 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

8. እንደ ሕልም በሮ ይጠፋል፤ አይገኝምም፤እንደ ሌሊትም ራእይ በቅጽበት ያልፋል።

9. ቀድሞ ያየው ዐይን ዳግመኛ አያየውም፤የነበረበትም ቦታ ከእንግዲህ አይመለከተውም።

10. ልጆቹ ለድኾች ካሣ መክፈል አለባቸው፤እጆቹም ሀብቱን መልሰው መስጠት ይገባቸዋል።

11. ዐጥንቱን የሞላው የወጣትነት ብርታት፣ከእርሱ ጋር በዐፈር ውስጥ ይተኛል።

12. “ክፋት በአፉ ውስጥ ቢጣፍጥ፣ከምላሱም በታች ቢደብቀው፣

13. አውጥቶ ለመጣል እየሳሳ፣በአፉ ውስጥ ቢያቈየው፣

14. ምግቡ በሆዱ ውስጥ ይመራል፤በውስጡም እንደ እባብ መርዝ ይሆናል።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኢዮብ 20