ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኢዮብ 20:6-11 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

6. እስከ ሰማይ ከፍ ከፍ ቢልም፣ዐናቱም ደመናትን ቢነካ፣

7. እንደ ኵበት ለዘላለም ይጠፋል፤ቀድሞ ያዩትም፣ ‘የት ገባ?’ ይላሉ።

8. እንደ ሕልም በሮ ይጠፋል፤ አይገኝምም፤እንደ ሌሊትም ራእይ በቅጽበት ያልፋል።

9. ቀድሞ ያየው ዐይን ዳግመኛ አያየውም፤የነበረበትም ቦታ ከእንግዲህ አይመለከተውም።

10. ልጆቹ ለድኾች ካሣ መክፈል አለባቸው፤እጆቹም ሀብቱን መልሰው መስጠት ይገባቸዋል።

11. ዐጥንቱን የሞላው የወጣትነት ብርታት፣ከእርሱ ጋር በዐፈር ውስጥ ይተኛል።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኢዮብ 20