ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኢዮብ 20:5-19 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

5. የኀጢአተኞች መፈንጨት ለአጭር ጊዜ፣የክፉዎችም ደስታ ለቅጽበት መሆኑን አታውቅምን?

6. እስከ ሰማይ ከፍ ከፍ ቢልም፣ዐናቱም ደመናትን ቢነካ፣

7. እንደ ኵበት ለዘላለም ይጠፋል፤ቀድሞ ያዩትም፣ ‘የት ገባ?’ ይላሉ።

8. እንደ ሕልም በሮ ይጠፋል፤ አይገኝምም፤እንደ ሌሊትም ራእይ በቅጽበት ያልፋል።

9. ቀድሞ ያየው ዐይን ዳግመኛ አያየውም፤የነበረበትም ቦታ ከእንግዲህ አይመለከተውም።

10. ልጆቹ ለድኾች ካሣ መክፈል አለባቸው፤እጆቹም ሀብቱን መልሰው መስጠት ይገባቸዋል።

11. ዐጥንቱን የሞላው የወጣትነት ብርታት፣ከእርሱ ጋር በዐፈር ውስጥ ይተኛል።

12. “ክፋት በአፉ ውስጥ ቢጣፍጥ፣ከምላሱም በታች ቢደብቀው፣

13. አውጥቶ ለመጣል እየሳሳ፣በአፉ ውስጥ ቢያቈየው፣

14. ምግቡ በሆዱ ውስጥ ይመራል፤በውስጡም እንደ እባብ መርዝ ይሆናል።

15. የዋጠውን ሀብት ይተፋል፤እግዚአብሔርም መልሶ ከሆዱ ያወጣዋል።

16. የእባብ መርዝ ይጠባል፤የእፉኝትም ምላስ ይገድለዋል።

17. ማርና ቅቤ በሚያፈሱ ጅረቶች፣በወንዞችም አይደሰትም።

18. የለፋበትን ሳይበላው ይመልሳል፤ከንግዱም ባገኘው ትርፍ አይደሰትም፤

19. ድኾችን በመጨቈን ባዶአስቀርቶአቸዋልና፣ ያልሠራውንም ቤት ነጥቆአል።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኢዮብ 20