ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኢዮብ 20:23-29 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

23. ሆዱን በሞላ ጊዜ፣እግዚአብሔር የሚነድ ቍጣውን ይሰድበታል፤መዓቱንም ያወርድበታል።

24. ከብረት መሣሪያ ቢሸሽም፣የናስ ቀስት ይወጋዋል።

25. ቀስቱን ከጀርባው፣የሚያብለጨልጨውንም ጫፍ ከጒበቱ ይመዛል፤ፍርሀትም ይይዘዋል፤

26. ሀብቱ ለድቅድቅ ጨለማ ተዳርጎአል፤ሰው ባላራገበው እሳት ይበላል፤በድንኳኑም ውስጥ የተረፈውን ይልሳል።

27. ሰማያት ኀጢአቱን ይገልጡበታል፤ምድርም ትነሣበታለች፤

28. በእግዚአብሔር የቍጣ ቀን ቤቱን ጐርፍ፣መኖሪያውንም ወራጅ ውሃ ይወስድበታል።

29. እግዚአብሔር ለኀጢአተኞች የወሰነው ዕድል ፈንታ፣ከአምላክም ዘንድ የተመደበላቸው ቋሚ ቅርስ ይህ ነው።”

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኢዮብ 20