ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኢዮብ 20:18-25 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

18. የለፋበትን ሳይበላው ይመልሳል፤ከንግዱም ባገኘው ትርፍ አይደሰትም፤

19. ድኾችን በመጨቈን ባዶአስቀርቶአቸዋልና፣ ያልሠራውንም ቤት ነጥቆአል።

20. “ክፉ ምኞቱ ዕረፍት አይሰጠውምሀብቱም ሊያድነው አይችልም።

21. ያለውን አሟጦ ስለሚበላ፣ዘላቂ ብልጽግና አይኖረውም።

22. በተድላ መካከል እያለ ጒስቍልና ይመጣበታል፤በከባድ መከራም ይዋጣል።

23. ሆዱን በሞላ ጊዜ፣እግዚአብሔር የሚነድ ቍጣውን ይሰድበታል፤መዓቱንም ያወርድበታል።

24. ከብረት መሣሪያ ቢሸሽም፣የናስ ቀስት ይወጋዋል።

25. ቀስቱን ከጀርባው፣የሚያብለጨልጨውንም ጫፍ ከጒበቱ ይመዛል፤ፍርሀትም ይይዘዋል፤

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኢዮብ 20