ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኢዮብ 20:17-23 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

17. ማርና ቅቤ በሚያፈሱ ጅረቶች፣በወንዞችም አይደሰትም።

18. የለፋበትን ሳይበላው ይመልሳል፤ከንግዱም ባገኘው ትርፍ አይደሰትም፤

19. ድኾችን በመጨቈን ባዶአስቀርቶአቸዋልና፣ ያልሠራውንም ቤት ነጥቆአል።

20. “ክፉ ምኞቱ ዕረፍት አይሰጠውምሀብቱም ሊያድነው አይችልም።

21. ያለውን አሟጦ ስለሚበላ፣ዘላቂ ብልጽግና አይኖረውም።

22. በተድላ መካከል እያለ ጒስቍልና ይመጣበታል፤በከባድ መከራም ይዋጣል።

23. ሆዱን በሞላ ጊዜ፣እግዚአብሔር የሚነድ ቍጣውን ይሰድበታል፤መዓቱንም ያወርድበታል።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኢዮብ 20