ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኢዮብ 20:11-16 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

11. ዐጥንቱን የሞላው የወጣትነት ብርታት፣ከእርሱ ጋር በዐፈር ውስጥ ይተኛል።

12. “ክፋት በአፉ ውስጥ ቢጣፍጥ፣ከምላሱም በታች ቢደብቀው፣

13. አውጥቶ ለመጣል እየሳሳ፣በአፉ ውስጥ ቢያቈየው፣

14. ምግቡ በሆዱ ውስጥ ይመራል፤በውስጡም እንደ እባብ መርዝ ይሆናል።

15. የዋጠውን ሀብት ይተፋል፤እግዚአብሔርም መልሶ ከሆዱ ያወጣዋል።

16. የእባብ መርዝ ይጠባል፤የእፉኝትም ምላስ ይገድለዋል።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኢዮብ 20