ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኢዮብ 20:1-9 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. ናዕማታዊውም ሶፋር እንዲህ ሲል መለሰ፤

2. “እጅግ ታውኬአለሁና፣ሐሳቤ መልስ እንድሰጥ ይጐተጒተኛል።

3. የሚያቃልለኝን ንግግር ሰምቼአለሁ፤መልስም እሰጥ ዘንድ መንፈሴ ገፋፋኝ።

4. “ሰው በምድር ላይ ከተቀመጠ ጊዜ ጀምሮ፣ከጥንቱ እንዴት እንደ ነበረ ታውቃለህን?

5. የኀጢአተኞች መፈንጨት ለአጭር ጊዜ፣የክፉዎችም ደስታ ለቅጽበት መሆኑን አታውቅምን?

6. እስከ ሰማይ ከፍ ከፍ ቢልም፣ዐናቱም ደመናትን ቢነካ፣

7. እንደ ኵበት ለዘላለም ይጠፋል፤ቀድሞ ያዩትም፣ ‘የት ገባ?’ ይላሉ።

8. እንደ ሕልም በሮ ይጠፋል፤ አይገኝምም፤እንደ ሌሊትም ራእይ በቅጽበት ያልፋል።

9. ቀድሞ ያየው ዐይን ዳግመኛ አያየውም፤የነበረበትም ቦታ ከእንግዲህ አይመለከተውም።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኢዮብ 20