ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኢዮብ 20:1-5 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. ናዕማታዊውም ሶፋር እንዲህ ሲል መለሰ፤

2. “እጅግ ታውኬአለሁና፣ሐሳቤ መልስ እንድሰጥ ይጐተጒተኛል።

3. የሚያቃልለኝን ንግግር ሰምቼአለሁ፤መልስም እሰጥ ዘንድ መንፈሴ ገፋፋኝ።

4. “ሰው በምድር ላይ ከተቀመጠ ጊዜ ጀምሮ፣ከጥንቱ እንዴት እንደ ነበረ ታውቃለህን?

5. የኀጢአተኞች መፈንጨት ለአጭር ጊዜ፣የክፉዎችም ደስታ ለቅጽበት መሆኑን አታውቅምን?

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኢዮብ 20