ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኢዮብ 19:8-15 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

8. እንዳላልፍ መንገዴን ዘግቶአል፤መሄጃዬንም በጨለማ ጋርዶአል።

9. ክብሬን ገፍፎኛል፤ዘውዴንም ከራሴ ላይ ወስዶአል።

10. እስክወገድ ድረስ በሁሉ አቅጣጫ አፈራርሶኛል፤ተስፋዬንም እንደ ዛፍ ነቅሎታል።

11. ቍጣው በላዬ ነዶአል፤እንደ ጠላቱም ቈጥሮኛል።

12. ሰራዊቱ ገፍተው መጡ፤በዙሪያዬ ምሽግ ሠሩ፤ ድንኳኔንም ከበው ሰፈሩ።

13. “ወንድሞቼን ከእኔ አርቆአል፤ከሚያውቁኝም ተገለልሁ።

14. ዘመዶቼ ትተውኛል፤ወዳጆቼም ረስተውኛል።

15. የቤቴ እንግዶችና ሴት አገልጋዮቼ እንደ መጻተኛ ቈጠሩኝ፤እንደ ባዕድም ተመለከቱኝ፤

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኢዮብ 19