ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኢዮብ 19:16-20 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

16. አገልጋዬን ብጣራ፣በአንደበቴም ብለምነው፣ አይመልስልኝም።

17. እስትንፋሴ ለሚስቴ እንኳ የሚያስጠላት ሆነ፤የገዛ ወንድሞቼም ተጸየፉኝ።

18. ሕፃናት እንኳ ይንቁኛል፤ባዩኝም ቍጥር ያላግጡብኛል።

19. የቅርብ ወዳጆቼ ሁሉ ተጸየፉኝ፤የምወዳቸውም በላዬ ተነሡ፤

20. ቈዳና ዐጥንት ብቻ ሆኜ ቀረሁ፤ድድ ብቻ ቀርቶልኝ አመለጥሁ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኢዮብ 19