ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኢዮብ 19:15-27 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

15. የቤቴ እንግዶችና ሴት አገልጋዮቼ እንደ መጻተኛ ቈጠሩኝ፤እንደ ባዕድም ተመለከቱኝ፤

16. አገልጋዬን ብጣራ፣በአንደበቴም ብለምነው፣ አይመልስልኝም።

17. እስትንፋሴ ለሚስቴ እንኳ የሚያስጠላት ሆነ፤የገዛ ወንድሞቼም ተጸየፉኝ።

18. ሕፃናት እንኳ ይንቁኛል፤ባዩኝም ቍጥር ያላግጡብኛል።

19. የቅርብ ወዳጆቼ ሁሉ ተጸየፉኝ፤የምወዳቸውም በላዬ ተነሡ፤

20. ቈዳና ዐጥንት ብቻ ሆኜ ቀረሁ፤ድድ ብቻ ቀርቶልኝ አመለጥሁ።

21. “ወዳጆቼ ሆይ፤ ራሩልኝ፤የእግዚአብሔር እጅ መታኛለችና ዕዘኑልኝ።

22. እግዚአብሔር እንዳሳደደኝ ለምን ታሳድዱኛላችሁ?አሁንም ሥጋዬ አልበቃችሁምን?

23. “ምነው ቃሌ በተጻፈ ኖሮ!በመጽሐፍም በታተመ!

24. ምነው በብረትና በእርሳስ በተጻፈ ኖሮ!በዐለትም ላይ በተቀረጸ!

25. የሚቤዠኝ ሕያው እንደሆነ፣በመጨረሻም በምድር ላይ እንደሚቆም ዐውቃለሁ።

26. ቈዳዬ ቢጠፋም፣ከሥጋዬ ብለይም፣ እግዚአብሔርን አየዋለሁ፤

27. ሌላ ሳይሆን እኔው በገዛ ዐይኔ፣እኔ ራሴ አየዋለሁ፤ልቤ በውስጤ ምንኛ በጉጉት ዛለ!

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኢዮብ 19