ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኢዮብ 19:11-23 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

11. ቍጣው በላዬ ነዶአል፤እንደ ጠላቱም ቈጥሮኛል።

12. ሰራዊቱ ገፍተው መጡ፤በዙሪያዬ ምሽግ ሠሩ፤ ድንኳኔንም ከበው ሰፈሩ።

13. “ወንድሞቼን ከእኔ አርቆአል፤ከሚያውቁኝም ተገለልሁ።

14. ዘመዶቼ ትተውኛል፤ወዳጆቼም ረስተውኛል።

15. የቤቴ እንግዶችና ሴት አገልጋዮቼ እንደ መጻተኛ ቈጠሩኝ፤እንደ ባዕድም ተመለከቱኝ፤

16. አገልጋዬን ብጣራ፣በአንደበቴም ብለምነው፣ አይመልስልኝም።

17. እስትንፋሴ ለሚስቴ እንኳ የሚያስጠላት ሆነ፤የገዛ ወንድሞቼም ተጸየፉኝ።

18. ሕፃናት እንኳ ይንቁኛል፤ባዩኝም ቍጥር ያላግጡብኛል።

19. የቅርብ ወዳጆቼ ሁሉ ተጸየፉኝ፤የምወዳቸውም በላዬ ተነሡ፤

20. ቈዳና ዐጥንት ብቻ ሆኜ ቀረሁ፤ድድ ብቻ ቀርቶልኝ አመለጥሁ።

21. “ወዳጆቼ ሆይ፤ ራሩልኝ፤የእግዚአብሔር እጅ መታኛለችና ዕዘኑልኝ።

22. እግዚአብሔር እንዳሳደደኝ ለምን ታሳድዱኛላችሁ?አሁንም ሥጋዬ አልበቃችሁምን?

23. “ምነው ቃሌ በተጻፈ ኖሮ!በመጽሐፍም በታተመ!

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኢዮብ 19