ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኢዮብ 16:5-11 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

5. ይልቁንም አንደበቴ ባበረታታችሁ፣የከንፈሬም ማጽናናት ባሳረፋችሁ ነበር።

6. “ብናገር ሕመሜ አይሻለኝም፤ዝም ብልም አይተወኝም።

7. እግዚአብሔር ሆይ አሁንስ አድክመኸኛል፤ወገኖቼንም ሁሉ አጥፍተሃል።

8. ጭምትርትር ያደረግኸኝ ምስክር ሆኖብኛል፣ዐጥንቴን ያወጣው ክሳቴም ያጋልጠኛል።

9. በቍጣው ሰነጠቀኝ፤ በጥላቻው አስጨነቀኝ፣ጥርሱን ነከሰብኝ፤ባላጋራዬ ክፉ ዐይኑን ተከለብኝ።

10. ሰዎች በፌዝ አፋቸውን ከፈቱብኝ፤በንቀት ጒንጬን ጠፈጠፉኝ፤በአንድነትም በላዬ ተሰበሰቡ።

11. እግዚአብሔር ለክፉዎች አሳልፎ ሰጠኝ፤በጠማሞችም እጅ ጣለኝ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኢዮብ 16