ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኢዮብ 16:4-9 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

4. እናንተ በእኔ ስፍራ ብትሆኑ ኖሮ፣እኔም እንደ እናንተ መናገር እችል ነበር፤ቃላት አሳክቼ በመናገር፣በእናንተ ላይ ራሴን መነቅነቅ በቻልሁ ነበር።

5. ይልቁንም አንደበቴ ባበረታታችሁ፣የከንፈሬም ማጽናናት ባሳረፋችሁ ነበር።

6. “ብናገር ሕመሜ አይሻለኝም፤ዝም ብልም አይተወኝም።

7. እግዚአብሔር ሆይ አሁንስ አድክመኸኛል፤ወገኖቼንም ሁሉ አጥፍተሃል።

8. ጭምትርትር ያደረግኸኝ ምስክር ሆኖብኛል፣ዐጥንቴን ያወጣው ክሳቴም ያጋልጠኛል።

9. በቍጣው ሰነጠቀኝ፤ በጥላቻው አስጨነቀኝ፣ጥርሱን ነከሰብኝ፤ባላጋራዬ ክፉ ዐይኑን ተከለብኝ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኢዮብ 16