ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኢዮብ 16:17-22 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

17. ነገር ግን በእጄ ዐመፅ አይገኝም፤ጸሎቴም ንጹሕ ነው።

18. “ምድር ሆይ፤ ደሜን አትሸፍኚ፤ጩኸቴም ማረፊያ አያግኝ!

19. አሁን እንኳ ምስክሬ በሰማይ አለ፤ጠበቃዬም በላይ በአርያም ይገኛል።

20. ወዳጆቼ በንቀት ቢመለከቱኝም፣ዐይኔ ወደ እግዚአብሔር ያነባል።

21. ሰው ለወዳጁ እንደሚማልድ፣በእግዚአብሔር ፊት የሚማልድ ሰው ምነው በተገኘ!

22. “ከጥቂት ዓመታት በኋላ፣ወደማልመለስበት መንገድ እሄዳለሁ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኢዮብ 16