ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኢዮብ 16:13-18 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

13. የእርሱ ቀስተኞች ከበቡኝ፤ያለ ርኅራኄ ኵላሊቴን ይበጣጥሳል፤ሐሞቴን መሬት ላይ ያፈሳል።

14. ደጋግሞ ይቀጠቅጠኛል፤እንደ ጦረኛም ተንደርድሮ ይመጣብኛል።

15. “በቈዳዬ ላይ ማቅ ሰፍቻለሁ፤ክብሬን በዐፈር ውስጥ ቀብሬአለሁ።

16. ፊቴ ከልቅሶ የተነሣ ቀልቶአል፤ጨለማም በዐይኖቼ ቆብ ላይ ዐርፎአል፤

17. ነገር ግን በእጄ ዐመፅ አይገኝም፤ጸሎቴም ንጹሕ ነው።

18. “ምድር ሆይ፤ ደሜን አትሸፍኚ፤ጩኸቴም ማረፊያ አያግኝ!

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኢዮብ 16