ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኢዮብ 16:12-22 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

12. በሰላም እኖር ነበር፤ እርሱ ግን ሰባበረኝ፤ዐንገቴን ይዞ አደቀቀኝ፤ማነጣጠሪያ ዒላማው አደረገኝ፤

13. የእርሱ ቀስተኞች ከበቡኝ፤ያለ ርኅራኄ ኵላሊቴን ይበጣጥሳል፤ሐሞቴን መሬት ላይ ያፈሳል።

14. ደጋግሞ ይቀጠቅጠኛል፤እንደ ጦረኛም ተንደርድሮ ይመጣብኛል።

15. “በቈዳዬ ላይ ማቅ ሰፍቻለሁ፤ክብሬን በዐፈር ውስጥ ቀብሬአለሁ።

16. ፊቴ ከልቅሶ የተነሣ ቀልቶአል፤ጨለማም በዐይኖቼ ቆብ ላይ ዐርፎአል፤

17. ነገር ግን በእጄ ዐመፅ አይገኝም፤ጸሎቴም ንጹሕ ነው።

18. “ምድር ሆይ፤ ደሜን አትሸፍኚ፤ጩኸቴም ማረፊያ አያግኝ!

19. አሁን እንኳ ምስክሬ በሰማይ አለ፤ጠበቃዬም በላይ በአርያም ይገኛል።

20. ወዳጆቼ በንቀት ቢመለከቱኝም፣ዐይኔ ወደ እግዚአብሔር ያነባል።

21. ሰው ለወዳጁ እንደሚማልድ፣በእግዚአብሔር ፊት የሚማልድ ሰው ምነው በተገኘ!

22. “ከጥቂት ዓመታት በኋላ፣ወደማልመለስበት መንገድ እሄዳለሁ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኢዮብ 16