ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኢዮብ 16:1-11 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. ኢዮብም እንዲህ ሲል መለሰ፤

2. “ይህን የሚመስል ብዙ ነገር ሰምቻለሁ፤እናንተ ሁላችሁ የምታስጨንቁ አጽናኞች ናችሁ።

3. ይህ ከንቱ ንግግር አያልቅምን?ትለፈልፍ ዘንድ የሚገፋፋህ ምንድን ነው?

4. እናንተ በእኔ ስፍራ ብትሆኑ ኖሮ፣እኔም እንደ እናንተ መናገር እችል ነበር፤ቃላት አሳክቼ በመናገር፣በእናንተ ላይ ራሴን መነቅነቅ በቻልሁ ነበር።

5. ይልቁንም አንደበቴ ባበረታታችሁ፣የከንፈሬም ማጽናናት ባሳረፋችሁ ነበር።

6. “ብናገር ሕመሜ አይሻለኝም፤ዝም ብልም አይተወኝም።

7. እግዚአብሔር ሆይ አሁንስ አድክመኸኛል፤ወገኖቼንም ሁሉ አጥፍተሃል።

8. ጭምትርትር ያደረግኸኝ ምስክር ሆኖብኛል፣ዐጥንቴን ያወጣው ክሳቴም ያጋልጠኛል።

9. በቍጣው ሰነጠቀኝ፤ በጥላቻው አስጨነቀኝ፣ጥርሱን ነከሰብኝ፤ባላጋራዬ ክፉ ዐይኑን ተከለብኝ።

10. ሰዎች በፌዝ አፋቸውን ከፈቱብኝ፤በንቀት ጒንጬን ጠፈጠፉኝ፤በአንድነትም በላዬ ተሰበሰቡ።

11. እግዚአብሔር ለክፉዎች አሳልፎ ሰጠኝ፤በጠማሞችም እጅ ጣለኝ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኢዮብ 16