ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኢዮብ 13:17-26 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

17. ቃሌን በጥንቃቄ አድምጡ፤እኔ የምለውንም ጆሮአችሁ በሚገባ ይስማ፤

18. እንግዲህ ጒዳዬን ይዤ ቀርቤአለሁ፤እንደሚፈርድልኝም ዐውቃለሁ።

19. ሊከሰኝ የሚችል አለ?ካለም፣ ዝም ብዬ ሞቴን እጠብቃለሁ።

20. “አምላክ ሆይ እነዚህን ሁለት ነገሮች ብቻ ስጠኝ፣ያን ጊዜ ከፊትህ አልሰወርም፤

21. እጅህን ከእኔ ላይ አንሣ፤በግርማህም አታስፈራራኝ፤

22. ከዚያ በኋላ ጥራኝ፤ እኔም እመልስልሃለሁ፤ወይም እኔ ልናገር፤ አንተ መልስልኝ።

23. በደሌና ኀጢአቴ ምን ያህል ነው?መተላለፌንና ኀጢአቴን አስታውቀኝ።

24. ፊትህን ለምን ትሰውራለህ?እንደ ጠላትህስ ለምን ትቈጥረኛለህ?

25. ነፋስ ያረገፈውን ቅጠል ታስጨንቃለህን?የደረቀውንስ እብቅ ታሳድዳለህን?

26. መራራ ነገር ትጽፍብኛለህ፤የወጣትነቴንም ኀጢአት ታወርሰኛለህ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኢዮብ 13