ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኢዮብ 13:14-27 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

14. ሥጋዬን በጥርሴ፣ሕይወቴንም በእጄ ለምን እይዛለሁ?

15. ቢገድለኝም እንኳ በእርሱ ተስፋ አደርጋለሁ፤ስለ መንገዴም ፊት ለፊት እከራከረዋለሁ።

16. ኀጢአተኛ በእርሱ ፊት መቅረብ ስለማይችል፤ይህ ድፍረቴ ለመዳኔ ይሆናል።

17. ቃሌን በጥንቃቄ አድምጡ፤እኔ የምለውንም ጆሮአችሁ በሚገባ ይስማ፤

18. እንግዲህ ጒዳዬን ይዤ ቀርቤአለሁ፤እንደሚፈርድልኝም ዐውቃለሁ።

19. ሊከሰኝ የሚችል አለ?ካለም፣ ዝም ብዬ ሞቴን እጠብቃለሁ።

20. “አምላክ ሆይ እነዚህን ሁለት ነገሮች ብቻ ስጠኝ፣ያን ጊዜ ከፊትህ አልሰወርም፤

21. እጅህን ከእኔ ላይ አንሣ፤በግርማህም አታስፈራራኝ፤

22. ከዚያ በኋላ ጥራኝ፤ እኔም እመልስልሃለሁ፤ወይም እኔ ልናገር፤ አንተ መልስልኝ።

23. በደሌና ኀጢአቴ ምን ያህል ነው?መተላለፌንና ኀጢአቴን አስታውቀኝ።

24. ፊትህን ለምን ትሰውራለህ?እንደ ጠላትህስ ለምን ትቈጥረኛለህ?

25. ነፋስ ያረገፈውን ቅጠል ታስጨንቃለህን?የደረቀውንስ እብቅ ታሳድዳለህን?

26. መራራ ነገር ትጽፍብኛለህ፤የወጣትነቴንም ኀጢአት ታወርሰኛለህ።

27. እግሬን በእግር ግንድ ታጣብቃለህ፤ውስጥ እግሬም ላይ ምልክት አድርገህ፣ዱካዬን አጥብቀህ ትከታተላለህ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኢዮብ 13