ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኢዮብ 13:14-19 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

14. ሥጋዬን በጥርሴ፣ሕይወቴንም በእጄ ለምን እይዛለሁ?

15. ቢገድለኝም እንኳ በእርሱ ተስፋ አደርጋለሁ፤ስለ መንገዴም ፊት ለፊት እከራከረዋለሁ።

16. ኀጢአተኛ በእርሱ ፊት መቅረብ ስለማይችል፤ይህ ድፍረቴ ለመዳኔ ይሆናል።

17. ቃሌን በጥንቃቄ አድምጡ፤እኔ የምለውንም ጆሮአችሁ በሚገባ ይስማ፤

18. እንግዲህ ጒዳዬን ይዤ ቀርቤአለሁ፤እንደሚፈርድልኝም ዐውቃለሁ።

19. ሊከሰኝ የሚችል አለ?ካለም፣ ዝም ብዬ ሞቴን እጠብቃለሁ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኢዮብ 13